የኢትዮጵያውያን ብልጽግና ሳናረጋግጥ አንተኛም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያውያን ብልጽግና ሳናረጋግጥ አንተኛም አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ እና የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ መሰረተ ድንጋይ ባስቀመጡበት ወቅት እንዳሉት÷ ኢትዮጵያውያን የብልጽግና ደረጃ ላይ ለማድረስ ስራችንን በትጋት እንጀምራለን ተግተንም እንጨርሳለን።
ተግተን ጀምረን ተግተን እንድንጨርስ፤ ተግተው የሚተቹ እና የሚዋሹ ያስፈልጋሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ እነሱ ይዋሻሉ እኛ እንሰራለን፤ እነሱ ያወራሉ እኛ እንከናወናለን በስራዎቻችን ሁሉ ኢትዮጵያን ከፍ እናደርጋለን ብለዋል።
ሕዳሴ በተመረቀበት ወቅት እስከ 30 ቢሊየን ዶላር የሚጠጉ ትልልቅ ፕሮጀክቶች እንደሚጀመሩ መናገራቸውን አስታውሰው÷ እነዚህ ፕሮጀክቶች ተጠንተው፣ ዝግጅት ተደርጎባቸው አና የሃብት ምንጭ ተለይቶ ካለምንም ጥርጥር በሚቀጥሉት አምስትና ስድስት ዓመታት የሚፈጸሙ ይሆናሉ ነው ያሉት።
ከፕሮጀክቶቹ መካከል በዛሬው ዕለት የ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ቶን ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ፣ እጅግ ግዙፍ የሆነ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ መጀመራቸውን ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም ከካሉብ የተፈጥሮ ጋዝን ወደ ጎዴ የሚያጓጉዝ ከ100 ኪሎ ሜትር በላይ የማስተላለፊያ ቱቦ ፕሮጀክት አንዱ መሆኑን አንስተው÷ የፋብሪካው የመጀመሪያ ዙር ስራ ጀምሯልም ነው ያሉት።
እንዲሁም ከ5 እስከ 7 ቢሊየን ዲላር ወጪ የሚደረግባቸው የኒውክለር ፕላንት ፕሮጀክቶች መፈረማቸውን አንስተው÷ በአየር መንገድ ዘርፍም ወደ 10 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ፕሮጀክት መጀመሩን ተናግረዋል።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!