Fana: At a Speed of Life!

ኢሬቻ የሰላም፣ የምስጋና እና አብሮነት የሚጸናበት በዓል ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ኢሬቻ ሰላም፣ ምስጋና እና አብሮነት የሚጸናበት በዓል ነው አሉ።

7ኛው የኢሬቻ ፎረም በቢሾፍቱ ከተማ ሆረ ሀርሴዴ አዳራሽ “ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ይገኛል።

በፎረሙ ላይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጂጌ (ዶ/ር)፣የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማን፣ ሚኒስትሮች፣ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በመድረኩ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤ በክልሉ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሁሉም ዘርፎች ውጤታማ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት እየተከናወኑ የሚገኙ ወሳኝ ሀገራዊ የልማት ስራዎች ለመጪው ጊዜ መሠረት የሚጥሉ መሆናቸውን መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የባህል እሴቶችን በማጉላት ለቱሪዝም ዘርፉ ከፍታ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረው፤ ኢሬቻ ሰላም፣ ምስጋና እና አብሮነት የሚጸናበት በዓል ነው ብለዋል።

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ነገ መስከረም 24 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሆረ ፊንፊኔ እንዲሁም ከነገ ወዲያ እሑድ መስከረም 25 ቀን 2018 ዓ.ም በቢሾፍቱ ሆረ ሀርሰዲ “ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.