Fana: At a Speed of Life!

ህዝባችን የተቃና አገልግሎት እና ሰላም እንዲያገኝ ተግተን እንሰራለን – አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ህዝባችን የተቃና አገልግሎት እና ሰላም እንዲያገኝ ተግተን እንሰራለን አሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ።

አቶ አረጋ የባሕር ዳር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ስራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት÷ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተተገበሩ ካሉ በርካታ የተቋማት ማሻሻያ ፕሮግራሞች አንዱ የሆነው የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ወሳኝ ሚና የሚጫወት ነው።

በሚቀጥሉት ቀናት የጎንደር እና ደሴ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ስራ እንደሚጀምር ገልጸው÷ ማዕከሉ በሌሎች ከተሞችም መስፋፋቱን ይቀጥላል ብለዋል።

የአንድ ማዕከል አገልግሎት ህዝቡን ለአገልግሎት ቅርብ እንዲሆን በማድረግ በዘመናዊ መንገድ አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያደርግና ህዝብ የላቀ አገልግሎት ማግኘት አለበት የሚል የመንግሥት ጽኑ የሪፎርም ውሳኔ ውጤት እንደሆነ ጠቁመዋል።

በአንዳንድ ተቋማት ላይ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን በመቀነስ ረገድ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አንስተው÷ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት በመዘርጋት የዜጎችን ኑሮ እንደሚያሻሽል፣ ኢንቨስትመንትን እንደሚያሳልጥና የሀገርና የክልሉን እድገት እንደሚያፋጥን አስረድተዋል።

ህዝብን ማገልገል ግዴታ መሆኑን መገንዘብ እንደሚገባ እና የማዕከሉ አገልግሎት መስጫዎች ለሌሎች አርዓያ መሆን እንዳለባቸው ያሳሰቡት አቶ አረጋ÷ ዜጎች በቅርብ ርቀት ተመሰሳይ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ አገልጋይ መንግሥት መኖሩን ማስመስከር ያስፈልጋል ብለዋል።

በማዕከሉ ውስጥ የገቡ ተቋማትና ሠራተኞች የህዝቡን እሮሮ የሚቀርፉ፣ በላቀ አገልግሎት የሚጠቀሱ፣ ስማቸው በብልሹ አሰራር የማይጠቀሱ መሆን እንዳለባቸው ገልጸው÷ የህዝብን እርካታ የሚያረጋግጥ መሆኑን በተግባር ማሳየት ይገባልም ነው ያሉት።

የህዝብን ሀብት የሚመዘብሩና አገልግሎትን የሚያጓትቱ አካላትን ጸንተን እንደሚታገሉ እንዲሁም ህዝቡ ሌቦችን በመከላከልና በማጋለጥ ተባባሪነቱን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።

በለይኩን ዓለም

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.