Fana: At a Speed of Life!

አማራጭ የሌለው የዲጂታል ጉዞን ደህንነት ማስጠበቅ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዲጂታል ጉዟችንን ደህንነት ማስጠበቅ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው አሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ።

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተዘጋጀው 6ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር “የሳይበር ደህንነት – የዲጂታል ኢትዮጵያ መሰረት” በሚል መሪ ኃሳብ በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል።

በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ዓለምፀሐይ ጳውሎስ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዓለም ወደ ዲጂታል ሽግግር በገባችበት በዚህ ዘመን የሳይበር ደህንነት ርዕሰ ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

ሁሉም ባለድርሻ አካላት የዲጂታል ጉዟችንን ደህንነት ማስጠበቅ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን መረዳት አለበት ነው ያሉት።

የሳይበር ደህንነት አስፈላጊነትን በመገንዘብ ሁሉም የድርሻውን ለመወጣት ቁርጠኛ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ በበኩላቸው፤ የሳይበር ደህንነት ወር መከበር ዋና ዓላማ የዜጎች እና የተቋማትን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ከፍ ማድረግ ነው ብለዋል።

በመሆኑም የግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ መርሐ ግብሮች እንደሚከናወኑ ጠቁመዋል።

አስተዳደሩ በብቁ የሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ የተደራጀ ብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ማዕከል በማቋቋም በሀገር ላይ ይቃጡ የነበሩ ጥቃቶችን ሲከላከል መቆየቱን አንስተዋል።

እንደ ሀገር ዲጂታል ዘርፉ አንዱ የኢኮኖሚ ቁልፍ መሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሯ፥ ተቋማት በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች ያለባቸውን ክፍተት ለመሙላት እየተሰራ ነው ብለዋል።

የሳይበር ደህንነት የአንድ ተቋም አልያም ግለሰብ ኃላፊነት አለመሆኑን ጠቅሰው፥ ዜጎች የማህበራዊ ሚዲያና የሰው ሰራሽ አስተውሎት አሉታዊ ተጽዕኖዎችን በመከላከል ረገድ አርበኛ ሊሆኑ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.