ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ምርጫ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ምርጫ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት የእውቅናና ሽልማት መርሐ ግብር አካሄደ።
በመርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ የምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት፣ የጠቅላይ ም/ቤቱ አመራሮች፣ ዑለማዎች ተገኝተዋል።
ሼኽ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፥ ታሪካዊ የሆነው ምርጫ ሰላማዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲካሄድ መንግስት ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የ2017 ምርጫ ጳጉሜ 2/2017 ዓ.ም በስኬት መጠናቀቁ ይታወሳል።
በጀማል አህመድ