Fana: At a Speed of Life!

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ከአይ ኤም ኤፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኒጄል ክላርክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ተቋሙ ለኢትዮጵያን እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀው፥ ይህም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ፣ ለስራ እድል ፈጠራ እና የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል፡፡

ምክትል ዳይሬክተሩ በበኩላቸው የኢትዮጵያ የሪፎርም አጀንዳ ለሌሎች ሀገራት አርአያ እንደሚሆን ገልጸው አይኤምኤፍ የኢትዮጵያን ለውጥ ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም የሪፎርም ትግበራ ከፍተኛ ወጪ እንዳለው ጠቅሰው ተጨማሪ ፋይናንስ ለማሰባሰብ እንደ ዓለም ባንክ ካሉ የልማት አጋሮች ጋር ቀጣይነት ያለው ትብብር አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

በአዲስ አበባ ሊካሄድ በታቀደው ሶስተኛው የዓለም የገንዘብ ድርጅት ግምገማ ወቅት ሁለቱም ወገኖች ተቀራርበው ለመስራት በመስማማት ውይይታቸውን አጠናቅቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.