የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የዲጂታል ስርዓት አስጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተቋማዊ አሰራሩን በማዘመን ወቅቱን የጠበቀና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የዲጂታል ስርዓትን ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ፡፡
ሚኒስቴሩ ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያበለጸገውን ዲጂታል የሰነድና ማህደር አስተዳደርና ወረቀት አልባ የአሰራር ስርዓትን ዛሬ ይፋ አድርጓል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷ ሚኒስቴሩ የተቋማዊ ሪፎርም አካል የሆነ የዲጂታል አሰራር ትግበራ መጀመሩን ገልጸው÷ ለዚህም ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ዲጂታል ስርዓት ማልማቱን ተናግረዋል፡፡
የሰነድና ማህደር አስተዳደር ስርዓቱ በሚኒስቴሩ ከመዝገብ አያያዝ እስከ ሚሲዮኖች የመረጃ ለውውጥ ድረስ የነበረውን የወረቀት አሰራር በማስቀረት ፈጣንና ቀልጣፋ የአገልግሎት ስርዓት መፍጠር ያስችላል ብለዋል፡፡
ወቅቱን የዋጀ ስርዓት ዘመናዊ የሰነድ አያያዝ ሥርዓቱ ከመፍጠር ባለፈ ጊዜንና ወጪን እንደሚቆጥብ ጠቁመዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወሻዎች፣ ጥናቶችና ታሪካዊ ፋይዳ ያላቸው ትልልቅ ሰነዶች የመነጩበት ተቋም መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ የሶፍትዌር ስርዓቱ የተቋሙን ተሞክሮዎችና ታሪኮች በዘመናዊ መንገድ ለመሰነድ የጎላ አበርክቶ እንዳለው አንስተዋል፡፡
የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲና የውጭ ግንኙነት ልምድና አገልግሎት ለዲፕሎማቶች ለማሸጋገር የማይተካ ሚና እንዳለውም መግለፃቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡
ሚኒስቴሩ በዲጂታል የሰነድ አስተዳደር፣ በውስጥና በውጪ ግንኙነት እና በደብዳቤ ልውውጥ እንዲሁም በተቀላጠፈ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የጋራ አቅም ለመፍጠር ያለመ የወረቀት አልባ ስማርት አሰራርና የዲጂታል የሰነድ ልውውጥና አያያዝ ስርዓት ላይ ያተኮረ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!