Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የካቶሊክ የርዳታ ድርጅት የልማት ስራዎችን አደነቁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የካቶሊክ የርዳታ ድርጅት (ሲ አር ኤስ) በኢትዮጵያ እያከናወናቸው ያሉትን የልማት ስራዎች አድንቀዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ታዬ ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ሱራፌል እና ከድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሻን ካላሃን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ የካቶሊክ የርዳታ ድርጅት በኢትዮጵያ በተለይም አርሶ እና አርብቶ አደሮችን በመደገፍ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡
ድርጅቱ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀው፥ በቀጣይም ለሚያከናውናቸው ተግባራት መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.