Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት የተማሪዎች ውጤት እየተሻሻለ ነው – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተከናወኑ ተግባራት በተማሪዎች ውጤት ላይ መሻሻሎች እየታዩ ነው አሉ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ።
“የትምህርት ፍትሃዊነትና ጥራት ለትውልድ ግንባታ” በሚል መሪ ሃሳብ 14ኛው ክልል አቀፍ የትምህርት ጉባዔ በጋምቤላ ከተማ እየተካሄደ ነው።
ሚኒስትሩ በጉባዔው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የሀገር እድገትና ስልጣኔ እውን የሚሆነው በሥነ ምግባርና በክህሎት የታነፀ ትውልድ ማፍራት ሲቻል ነው።
ዘላቂ ልማትና እድገት እንዲረጋገጥ ጥራት ያለው ትምህርትን ተደራሽ በማድረግ በራሱ የሚተማመን ዜጋ መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል።
በዚህም ባለፉት የለውጥ ዓመታት የትምህርት ጥራትንና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት በተለይ በተማሪዎች ውጤት ላይ መሻሻሎች እየታዩ መሆኑን ገልጸዋል።
በጋምቤላ ክልልም በተማሪዎች ውጤት ላይ ለውጥ መኖሩን ጠቅሰው÷ ለውጡን ይበልጥ ለማጠናከር አመራሩ በላቀ ቁርጠኝነት እንዲሰራ አስገንዝበዋል።
የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ በትምህርት ሽፋን የተሻለ ስኬት መመዝገቡን ገልጸው÷ ጥራትን በማረጋገጥ ረገድ ውስንነቶች አሉ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በክልሉ በትምህርት ሽፋን የተመዘገበውን ውጤት በጥራት ለመድገም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ባሳተፈ መልኩ ጠንክሮ መስራት ይገባል ነው ያሉት፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.