የአዲስ አበባ ከተማ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ መካሄድ ጀምሯል።
በመድረኩ በሩብ ዓመቱ የታቀዱ እና የ90 ቀን አበይት ተግባራት የደረሱበት ደረጃ እንደሚገመገም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡
በመዲናዋ የተለየ ትኩረት የሚሹ ተግባራት ተለይተው ቀጣይ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡም ነው የገለጹት፡፡
በተጨማሪም የተገኙ ውጤታማ አፈጻጸሞች ተጠናክረው የሚቀጥሉበትና የታዩ ጉድለቶች የሚታረሙበት የግምገማ መድረክ እንደሚሆን ከንቲባዋ አመልክተዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!