Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሕልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሕልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልዕክት÷ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ /ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በማረፋቸው ኀዘን ተሰምቶኛል ብለዋል።

 ሐጂ ዑመር በአመራር ዘመናቸው የተለያዩ ወገኖች ወደ አንድነት እንዲመጡ እና የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሕግ ዕውቅና እንዲኖረው ያደረጉትን አስተዋጽኦ ሁሌም እናስታውሰዋለን ሲሉም ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (/) ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.