በባንግላዲሽ አውሮፕላን ማረፊያ በደረሰ የእሳት አደጋ የ1 ቢሊየን ዶላር ኪሳራ ደረሰ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በባንግላዲሽ አውሮፕላን ማረፊያ በደረሰ የእሳት አደጋ 1 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ጉዳት ደርሷል።
በአውሮፕላን ማረፊያው ጉዳት በደረሰበት የሎጅስቲክስ ማዕከል ጨርቆች፣ መድሐኒቶች፣ ኬሚካሎችና ሌሎች እቃዎች ተከማችተው የነበረ ሲሆን፥ በአልባሳት እና ጥሬ እቃዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።
27 ሰዓታት በፈጀው የእሳት ቃጠሎውን የማጥፋት ሂደት 35 ሰዎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፥ በአደጋው ምክንያት በረራዎች ለጊዜው መቋረጣቸውም ነው የተገለጸው።
የእሳት አደጋውን መንስኤ ለማጣራት ምርመራ እየተከናወነ ሲሆን፥ አደጋው በቀጣይ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ሊጎዳ እንደሚችል የሀገሪቱን የአልባሳት አምራቾችና ላኪዎች ማህበር ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ባንግላዲሽ ከቻይና በመቀጠል በዓለም ሁለተኛዋ የጨርቃ ጨርቅ አቅራቢ መሆኗን የጠቀሰው ዘገባው፥ ዘርፉ በዓመት 40 ቢሊየን ዶላር ገቢ በማመንጨት ከሀገሪቱ አጠቃላይ ምርት 10 በመቶውን እንደሚይዝ አመልክቷል፡፡
ባሳለፍነው ቅዳሜ የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ በሀገሪቱ በአንድ ሳምንት ውስጥ የተከሰተ ሦስተኛው ከባድ የእሳት ቃጠሎ ሲሆን፥ በመጋዘን ላይ በደረሰ ሌላ ቃጠሎ ቢያንስ 16 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል፡፡
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!