ለተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስከሬን የሽኝት ሥነ ሥርዓት እየተከናወነ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስከሬን በሚሊኒዬም አዳራሽ የዱዓ እና ሽኝት ሥነ ሥርዓት እየተከናወነ ይገኛል።
በመርሐ ግብሩ የሃይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ ኡለማዎች፣ ደረሳዎች፣ ኡስታዞች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ከ50 ዓመታት በላይ በዘለቀ የአዲስ አበባ ቆይታ ቅዱስ ቁርዓንን ከ300 ጊዜ በላይ በትርጉም አስተምረዋል።
በ1967 ዓ.ም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ሲመሰረት የምክር ቤቱ አባልና የዑለማ ሊቀመንበር ነበሩ፡፡
ከ2010 መጋቢት እስከ ግንቦት ወር 2014 ዓ.ም ድረስ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱን በፕሬዚዳንትነት እንዲሁም የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ በመሆን አገልግለዋል፡፡