Fana: At a Speed of Life!

የተፈጥሮ ሃብትን በሚገባ ጥቅም ላይ ለማዋል መሰረተ ልማትን ማጠናከር ይገባል – አቶ ጌታቸው ረዳ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ያለንን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት በሚገባ ጥቅም ላይ ለማዋል መሰረተ ልማትን ማጠናከር ይገባል አሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሶፍ ዑመር ወግ በሚል ርዕስ ከቀድሞ እና በሥራ ላይ ካሉ አመራሮች ጋር መክረዋል፡፡

አቶ ጌታቸው ረዳ በዚህ ወቅት ÷ ሶፍ ዑመር ኢትዮጵያ ከምትኮራባቸው መልክዓ ምድር ውስጥ አንዱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሶፍ ዑመር ዋሻ መልክዓ ምድር ብቻ ሳይሆን ታሪክ እና ባህል ጭምር እንደሆነ በመመልከታቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡

ሰላምን ማስፈንና መሰረተ ልማትን መጠናከር የሚደጋገፉ ነገሮች መሆናቸው ጠቅሰው ÷ በአካባቢው ያለውን እምቅ ሃብት በሚገባ ለመጠቀም መሰረተ ልማትን ማስፋት ይገባል ብለዋል፡፡

ያለንን ተፈጥሮ ወደ ሃብት ለመቀየር መስራት ይገባል ያሉት አቶ ጌታቸው÷ በቀጣይ ችግሮችን ነቅሶ በመለየት በቅንጅት መስራት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በአካባቢው መልማት የሚችል መሬት እያለ በመሰረተ ልማት ችግር ሳቢያ እድሉን ማጣቱ የሚያስቆጭ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ያለውን ሃብት ተጠቅመን ሕዝቡ የተረጋጋ ኑሮ እንዲኖር ብሎም ከተረጂነት ተላቅቆ ሌሎችን መርዳት እንዲችል መስራት ይገባል ነው ያሉት፡፡

ካለፉት ስሕተቶች በመማር ያለውን ሃብትና አቅም በሚገባ ተጠቅሞ ከተሳራ ለውጥ መፍጠር እንደሚቻልም አስገንዝበዋል፡፡

አካባቢውን የቱሪስት መዳረሻነት ይበልጥ ለማጠናከር ባህሉን እና ታሪኩን በማስተሳሰር መስራት ይገባል ነው ያሉት፡፡

በባሌ ዞን የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው፤ መሰል ሥራዎችን በሌሎች አካባቢዎች ለመድገምም በትኩረትና በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.