በባሌ የሚሰራው የልማት ስራ ከኦሮሚያ አልፎ ለሀገርም ትልቅ ሚና ያለው ነው – ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በባሌ የሚሰራው የልማት ስራ ከኦሮሚያ አልፎ ለሀገርም ትልቅ ሚና ያለው ነው አሉ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የሶፍ ዑመር ወግ በሚል ርዕስ ከቀድሞ እና በሥራ ላይ ካሉ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷ ባሌን ከዚህ በፊት አውቃታለሁ ነገር ግን ዛሬ ላይ ያየሁት የነበራትን እና ያላትን እምቅ ሃብት የሚገልጹ ስራዎች ነው ብለዋል።
ከቀድሞ እና በሥራ ላይ ካሉ አመራሮች ጋር በመሆነው የሚደረገው ጉብኝት ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ያልተለመደና የሚደነቅ ሐሳብ መሆኑን አንስተው÷ የዚህ አካል በመሆናቸው ደስተኛ እንደሆኑ ተናግረዋል።
በባሌ የሚሰራው የልማት ስራ ከኦሮሚያ አልፎ ለሀገርም ትልቅ ሚና ያለው መሆኑን አመላክተዋል።
ሰሞኑን በባሌ በነበራቸው የሶስት ቀናት ጉብኝት መተባበር፣ በጋራ መስራት በዋነኛት ጠንካራ የመሪነት ሚና ደግሞ ምን ያህል እንደሆነ የተረዱበት እንደሆነም አጽንኦት ሰጥተዋል።
በሶስና አለማየሁ