የገጠር ኮሪደር ምርታማነትን ከማሳደግ ባሻገር ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ያረጋግጣል – ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) የገጠር ኮሪደር ልማት ምርታማነትን ከማሳደግ ባሻገር ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ያረጋግጣል አሉ፡፡
የገጠር ኮሪደር ልማት የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ስልጠና በደብረብርሃን ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመርሃ ግብሩ ላይ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የገጠር ቀበሌዎችን ለማዘመንና ለማሻሻል ትልቅ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ ይገኛል።
ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የገጠሩን ማህበረሰብ ሕይወት ለማሻሻል ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ተናግረዋል።
በዚህም የገጠሩን ማህበረሰብ ህይወት ለማሻሻል የገጠር ኮሪደር ልማትን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
የገጠር ኮሪደር ልማት ለሁለንተናዊ የክልሉ እድገት ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልጸው፤ የቴክኖሎጂ ትስስር ከመፍጠር እና ምርታማነትን ከማሳደግ ባሻገር ፍትሀዊ ተጠቃሚነትንም ያረጋግጣል ብለዋል፡፡
በኤልያስ ሹምዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!