Fana: At a Speed of Life!

ቤአኤካ በፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ሊያስገባ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃላ/የተ/የግል ማኅበር በፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ቤአኤካ ስምምነቱን ከቻይናው የመኪና አቅራቢ ሻክማን ኩባንያ ጋር የተፈራረመ ሲሆን÷ ኩባንያው በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ መኪኖችን ለቤአኤካ የሚያቀርብ የሚያቀርብ ይሆናል፤

በዚህም ቤአኤካ በፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በመቀበል ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚያስገባና በቅርቡም 150 ተሽከርካሪዎች እንደሚገቡ ተገልጿል።

በተጨማሪም ቤአኤካ በፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን መገጣጠሚያ ፋብሪካ ዝግጅት መጠናቀቁንና በመጀመሪያ ዙር 1 ሺህ 500 መኪኖችን ለመገጣጠም መታቀዱ በስምምነቱ ወቅት ተጠቁሟል።

በቅድስት አባተ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.