ኢትዮጵያ ጠንካራ የጤና ሥርዓትን ለመገንባት በትኩረት እየሰራች ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የተሳተፉበት ጥራት ያለውን የጤና አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የውይይት መድረክ በዓለም ባንክ እና የዓለም ጤና ድርጅት አዘጋጅነት ተካሂዷል፡፡
ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት÷ ኢትዮጵያ የጤና ዘርፉን ለማሻሻልና ጠንካራ የጤና ሥርዓትን ለመገንባት በትኩረት እየሰራች መሆኗን አብራርተዋል፡፡
በዚህም በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ አጽንዖት በመስጠት ማሕበረሰብ አቀፍ የጤና ኢንሹራንስ ማስፋፋት፣ በጤና ጥበቃ ኢትዮጵያን የቀጣናው መሪ ማድረግ፣ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት የዘርፉን ወጪ 20 በመቶ ማድረስ እንዲሁም የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደግን ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ መድኃኒት የማምረት አቅም እያሳደገች እንደሆነና ለአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ሀገራት መላክን ታሳቢ በማድረግ እየሰራች መሆኗን ተናግረዋል።
በመድረኩ ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፉ የጤና ተደራሽነት ፕሮግራም ከተመረጡት ስምንት ሀገራት መካከል እንደምትገኝም ይፋ ተደርጓል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!