የግሪሳ ወፍን ለመከላከል የኬሚካል ርጭት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር የተከሰተውን የግሪሳ ወፍ የመከላከል ሥራ እየተከናወነ ነው፡፡
በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የሰብል ልማት እና ጥበቃ ዳይሬክተር ማንደፍሮ አስላከ (ዶ/ር)÷ ምርታማነትን ከሚቀንሱ ነፍሳት ውስጥ የግሪሳ ወፍ ዋናው መሆኑን ተናግረዋል።
በወረርሽኝ መልክ የሚከሰቱ ነፍሳት በአጭር ጊዜ በሰፊ ቦታ ላይ የሚገኝን ሰብል በማውደም በምርታማነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርሱ አመልክተዋል፡፡
አሁን ላይ በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር እና ሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኙ አራት ቀበሌዎች የግሪሳ ወፍ መከሰቱን አብራርተዋል፡፡
የግሪሳ ወፉ 12 ማደሪያ ቦታዎች ተለይተዋል ያሉት ዳይሬክተሩ ÷በእነዚህ አካባቢዎች እስከ 16 ሚሊየን የሚገመት የግሪሳ ወፍ መኖሩን ጠቁመዋል፡፡
ችግሩን ለመቅረፍ ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመቀናጀት በማደሪያ ቦታዎች ላይ ከጥቅምት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የአውሮፕላን ርጭት እየተካሄደ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በተለይም ከፍተኛ የግሪሳ መንጋ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ቅድሚያ ተሰጥቶ ርጭት እየተደረገ ነው ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
የመከላከል ሥራው በፍጥነት በመጀመሩ በምርት ላይ ጉዳት አለመድረሱን ማንደፍሮ (ዶ/ር) አስገንዝበዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!