Fana: At a Speed of Life!

የጣና ፎረም በዛሬው ዕለት በባሕር ዳር ከተማ ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 11ኛው የጣና ፎረም በዛሬው ዕለት በባሕር ዳር ከተማ መካሄድ ይጀምራል፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ዘሪሁን አበበ እንዳሉት፥ ፎረሙ “አፍሪካ በተለዋዋጩ ሉላዊ ሥርዓት” በሚል መሪ ሀሳብ በሦስት መድረኮች ይካሄዳል።

የመጀመሪያው መድረክ በዛሬው ዕለት በባሕር ዳር የሚካሄድ ሲሆን÷ 2ኛው በአዲስ አባባ እንዲሁም 3ኛው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሳባ ይከናወናል ብለዋል።

በመድረኩ ላይ የሚሳተፉ የቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት ተወካዮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የባለብዙ ወገን ተቋማትና ልዩ መልዕክተኞች ባሕር ዳር ከተማ ገብተዋል።

በፎረሙ አፍሪካውያን በተለዋዋጩ የዓለም ሥርዓት ውስጥ ተዋናይ እንዲሆኑ የሚያስችል ምክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.