Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በዘንድሮ በጋ መስኖ 4 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ ይለማል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል በዘንድሮ በጋ መስኖ 4 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ ለማልማት ታቅዷል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ጌቱ ገመቹ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፤ በ2018 ዓ.ም የበጋ ወቅት የመስኖ ልማት ስራዎች አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል።

በዚህም የመስኖ አቅም ያላቸውን አካባቢዎች በማልማት ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸው፤ አርሶ አደሩን ጨምሮ የሚመለከታቸው ባለድርሻዎችን የማዘጋጀት የንቅናቄ ሥራ ተሰርቷል ብለዋል።

በዘንድሮ በጋ መስኖ 4 ሚሊየን ሄክታር መሬት በስንዴ ሰብል ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር ተገብቷል ያሉት አቶ ጌቱ ገመቹ፤ 600 ሺህ ኩንታል የምርጥ ዘር እና 3 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ መቅረቡን ጠቁመዋል።

እንዲሁም 29 ሺህ የውሃ መሳቢያ ፓምፕ ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን ገልጸው፤ ይህም ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል።

እስካሁን ድረስ 493 ሺህ 156 ሄክታር መሬት ታርሶ ከዚህ ውስጥ 238 ሺህ 336 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል።

በአቤል ነዋይ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

Facebook WMCC

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.