ስምረት ፓርቲ የምስረታ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ስምረት (ስምረት) ፓርቲ የምስረታ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል፡፡
የፓርቲው አደራጅ ኮሚቴ አስተባባሪ አቶ ጌታቸው ረዳ በጉባኤው ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፥ የትግራይን ህዝብ ህልውና ለማስጠበቅ መስራት አለብን ብለዋል።
ፓርቲው እስካሁን ከ5 ሺህ 600 በላይ አባላት መመዝገቡን ጠቅሰው፥ አባላቱ በምስረታ ጉባኤው ላይ መሳተፍ ቢፈልጉም በፀጥታ ችግር መምጣት እንዳልቻሉ አንስተዋል።
ፓርቲው የትግራይ ህዝብ በህወሓት እየደረሰበት ያለውን ጫና በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መመስረቱን የተገለጸ ሲሆን፥ ህወሓት ከሌሎች የውጪ አካላት ጋር በመቀናጀት በክልሉ ብሎም በሀገር ሰላም ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደረ ይገኛል ብለዋል።
እየተካሄደ ባለው ጉባኤ 256 አባላት ድምፅ በመስጠት እንደሚሳተፉ ተመላክቷል፡፡
ሌ/ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ በበኩላቸው ላለፉት 50 ዓመታት በላይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ አንድ አካል የነበረው ህወሓት የትግራይን ህዝብ የፖለቲካ መጠቀሚያ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለዚህም ስምረት ፓርቲ በኃይል ሳይሆን በሀሳብ ላይ የተመሰረተ ትግል ለማድረግ መመስረቱ የትግራይ ህዝብ ሰላም ፈላጊነትን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
በምስረታ ጉባኤው ላይ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ መለሰ ዓለሙ፥ ለኢትዮጵያ መፃኢ የብልፅግና ጉዞ ስምረት ፓርቲ ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል ነው ያሉት።
በነፃነት ፀጋይ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!