Fana: At a Speed of Life!

በሸገር ከተማ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሸገር ከተማ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የከተማዋ መንገድ ስራዎች ጽሕፈት ቤት።

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ዘላለም ቦጃ (ኢ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ የተለያዩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን በተያዘው በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ከእነዚህም ከገላን አራብሳ እስከ ኩራ ጅዳ ክፍለ ከተማ የሚደርስ የምዕራፍ አንድ የመንገድ ፕሮጀክት ስራ ተጠቃሽ መሆኑን አንስተው÷ ፕሮጀክቱ በ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በጀት እየተገነባ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

38 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የመንገድ ፕሮጀክቱ በሦስት ምዕራፍ እንደሚሰራና የቀለበት መንገድንም እንደሚያካትት ተናግረዋል።

የሸገር ከተማ አስተዳደር በ800 ሚሊየን ብር በጀት በኮዬ ፌጬ ክፍለ ከተማ ከሸገር ኢኒስቲትዩት ቴክኖሎጂ እስከ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚደርስ አዲስ የመንገድ ስራ መጀመሩንም አመላክተዋል።

የመንገድ ስራው 1 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 40 ሜትር ስፋት ያለውን የአስፋልት መንገድ እና ኮሪደር ያካተተ መሆኑን አንስተው÷ ከዚህ በፊት የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን በተያዘው በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ በፍጥነትና በጥራት እየተሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል።

በማሕበረሰቡ ዘንድ የሚነሱ የመሰረተ ልማትና የመንገድ ጥያቄዎችን ለመፍታት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝም ኃላፊው ገልጸዋል።

በታሪክ አዱኛ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.