Fana: At a Speed of Life!

የጣና ፎረም የባህር ዳር መድረክ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በባህርዳር ከተማ የተካሄደው 11ኛው የጣና ፎረም በስኬት ተጠናቅቋል አለ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ፡፡

የዋና ጠቅላይ መምሪያው አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ (ዶ/ር) የመድረኩ ተሳተፊ እንግዶች በከተማዋ የሰመረ ቆይታ እንዲኖራቸው ለማስቻል የጸጥታ የጋራ ግብረ ኀይል ተቋቁሞ በቂ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡

ይህም እንግዶች ከፎረሙ ጎን ለጎን ባሕር ዳር ከተማን እና በጣና ሐይቅ ላይ የተሠሩ ልማቶችን ተዘዋውረው እንዲያዩ እና ያማረ ቆይታ እንዲኖራቸው አስችሏል ነው ያሉት።

እንግዳ ወዳዱ የባሕር ዳር ከተማ ሕዝብ እንግዶቹን ተቀብሎ እሴቱን በጠበቀ መልኩ አስተናግዷል በማለት ገልጸው÷ ህዝቡ ላሳየው እንግዳ ተቀባይነት ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

መድረኩ ባህር ዳር ከተማ ያካበተችውን ዓለም አቀፍ መድረኮችን የማስተናገድ ብቃት ያስመሰከረ እንደሆነም መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል።

በቀጣይም እንዲህ ዓይነት ዓለም አቀፍ፣ አሕጉራዊ እና ሀገር አቀፍ ጉባኤዎች በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ለማከሄድ የሚያስችል አስተማማኝ አቅም መኖሩን አመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.