Fana: At a Speed of Life!

መንግስት ውስጣዊ ችግሮችን ተቋቁሞ ያከናወናቸው ስራዎች የሚደነቁ ናቸው – በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) መንግስት ውስጣዊ ችግሮችን ተቋቁሞ ያከናወናቸው የልማት ስራዎች የሚደነቁ ናቸው አሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ‘የሚኒስትሮች ምክር ቤት ምልከታ በኮይሻ’ በሚል ርዕስ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማ ውይይት በኮይሻ ግድብ ከሚኒስትሮች ጋር አድርገዋል።

በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት፤ የኮይሻ ፕሮጀክትን በጎበኘሁበት ወቅት ኢትዮጵያ ሰፊ የተፈጥሮ ሀብት እና ፀጋዎች ያላት ሀገር መሆኗን ተረድቻለሁ ብለዋል፡፡

የተፈጥሮ ሀብቱ ቀድሞም የነበረ ቢሆንም ጸጋዎችን ለይቶ እና ተረድቶ ማልማት የሚያስችል እይታ ባለመኖሩ በተገቢው መልኩ መልማት እንዳልቻለ አንስተዋል፡፡

አሁን ላይ ይህንን የተፈጥሮ ፀጋ መረዳት እና ማልማት የሚችል አመራር በመኖሩ በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ እና አዳዲስ መጀመር ተችሏል ብለዋል።

በተለይም የኮይሻ ፕሮጀክትን ጨምሮ የኢትዮጵያን የቱሪዝም ዘርፍ አንድ ርምጃ ከፍ ያደረጉ ፕሮጀክቶች መገንባታቸውን እና በዚህም የኢትዮጵያ የቱሪዝም ኢኮኖሚ እያደገ መምጣቱን አመላክተዋል፡፡

በሀገር ውስጥ ከተፈጠሩ ችግሮች አንፃር ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ገንብቶ ማጠናቀቅ አስቸጋሪ ቢሆንም መንግስት ችግሮችን በመቋቋም በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቁ የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.