ኢትዮጵያ ጉዞዋ ከትናንት እየተሻለ መጥቷል – ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ጉዞዋ ከትናንት እየተሻለ መጥቷል አሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማሕበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትር ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፡፡
‘የሚኒስትሮች ምክር ቤት ምልከታ በኮይሻ’ በሚል ርዕስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማ ውይይት በኮይሻ ግድብ ከሚኒስትሮች ጋር አድርገዋል።
ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በውይይቱ ወቅት፤ የ100 ቀናት ዕቅዱ ኢትዮጵያ ሁልጊዜ እያደገች እና እየተለወጠች እንደሆነ ያሳያል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጉዞ የማይቆም እና ሁሌም ታሪክ የሚጻፍበት መሆኑን ጠቅሰው፥ ጉዞዋ ትናንት ከነበረችበት እየተሻለ እና እየተለወጠ መጥቷል ነው ያሉት።