Fana: At a Speed of Life!

የኮሪደር ልማት የከተሞችን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ጉልህ ኢኮኖሚዊ ፋይዳ አለው – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ሥራዎች ዘመኑን የዋጁና የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ ናቸው አሉ በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ጋር የተጠናቀቀውን የሳር ቤት – ጀርመን አደባባይ- ጋርመንት እና ፉሪ አካባቢ የኮሪደር ልማት ሥራ ጎብኝተዋል።
አቶ አደም ጉብኝቱን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ÷ የሳር ቤት – ጀርመን አደባባይ – ጋርመንት እና ፉሪ አካባቢ የኮሪደር ልማት ሥራ እስካሁን በከተማዋ ከተከናወኑት በስፋቱ የላቀ ነው ብለዋል።
ከእያንዳንዱ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ትምህርት በመውሰድ የተሻለ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው÷ በመዲናዋ የተሰሩ የኮሪደር ልማት ሥራዎች የኢትዮጵያን ገጽታ የቀየሩ ናቸው ብለዋል።
የኮሪደር ልማት ሥራዎቹ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ እና ለዓለም ትምህርት የሰጡ መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት የተጀመሩትን የኮሪደር ልማት ሥራዎች በየደረጃው ያለው አመራር ተቀብሎ በቁርጠኝነት መተግበሩ ተጨባጭ ውጤት መምጣቱን አንስተዋል።
ሕዝቡም እያበረከተ ያለው ጉልህ አስተዋጽኦና ተሳትፎ እንዲሁም እየሰጠ ያለው ድጋፍ በኮሪደር ልማት የሚፈለገው ውጤት እንዲመጣ የራሱ ሚና አለው ነው ያሉት፡፡
የኮሪደር ልማት የከተሞችንና የሀገርን ገጽታ ከመቀየር ባሻገር ኢኮኖሚዊ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ጠቁመው÷ ዜጎች የመስሪያና የመሸጫ ቦታ እንዲያገኙና ፍትሐዊ የሃብት ክፍፍል እንዲፈጠር ማድረጉን ጠቅሰዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.