ሲዳማ ቡና ሀዋሳ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሁለተኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና ሀዋሳ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የሲዳማ ቡናን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ያሬድ ባዬህ በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡
ቀደም ብሎ ቀን 6 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከምድረ ገነት ሽረ ጋር ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡