የ23ኛው ዓለም ዋንጫ የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ23ኛው ዓለም ዋንጫ የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት በኒውዮርክ ሜትላይፍ ስታዲየም እየተካሄደ ነው።
ላለፉት 39 ቀናት በአሜሪካ፣ ካናዳና ሜክሲኮ ጣምራ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 23ኛው የዓለም ዋንጫ ስፔንና አርጀንቲና ምሽት 4 ሰዓት ላይ በሚያደርጉት የፍጻሜ ጨዋታ ይጠናቀቃል።
ከፍጻሜ ጨዋታው በፊትም የመዝጊያ ሥነ ሥርዓቱ በሜትላይፍ ስታዲየም በተለያዩ ሁነቶች በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በመርሐ ግብሩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት መሪዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ይታደማሉ፡፡