ቼልሲ በሰንደርላንድ ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ9ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቼልሲ በሰንደርላንድ 2 ለ1 ተሸንፏል፡፡
በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ ጨዋታውን ያደረገው ቼልስ በአሌሃንድሮ ጋርናቾ ግብ ሲመራ ቢቆይም ኢሲዶርና ታልቢ ለሰንደርላንድ ባስቆጠሯቸው ግቦች ተሸንፏል፡፡
በሌላ ጨዋታ ኒውካስል ዩናይትድ ፉልሃምን 2 ለ 1 ሲያሸንፍ ÷ የኒውካስልን ግቦች መርፊ እና ብሩኖ ጉማሬሽ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡