በቢሾፍቱ የሚሰራው አውሮፕላን ማረፊያ ከአፍሪካ ትልቁ ይሆናል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቢሾፍቱ የሚሰራው አውሮፕላን ማረፊያ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የሚያመጣና ከ100 ሚሊየን በላይ ተጓዦችን በዓመት የሚያስተናግድ በመሆኑ ከአፍሪካ ትልቁ አውሮፕላን ማረፊያ ይሆናል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በ6ኛ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ነው።
በቢሾፍቱ የሚሰራው አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ በቻ ሳይሆን ትልቁ የአውሮፕላን ማረፊያ ባለቤት ያደርገዋልም ነው ያሉት።
ይህ ግዙፍ የ10 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት ኢትዮጵያን በቀጣይነት የአፍሪካ የአቪዬሽን ማዕከል ሆና እንድትቀጥል ያደርጋታል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ለማዳበሪያ እና ነዳጅ የምታወጣው ወጪ ትልቁ እንደሆነ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷ እነዚህን መተካት ከተቻለ ከፍተኛ ሀብት ለልማት ማስቀረት እንደሚቻል አስረድተዋል።
ለዚህም ዳንጎቴ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የሚያለማው የማዳበሪያ ፋብሪካ 30 ሚሊየን ኩንታል ዩሪያ የሚያመርት መሆኑን አንስተዋል።
የቤት ግንባታ ፕሮጀክትን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የቤት ባለቤት እንዲሆን ማድረግ የሚቻል አለመሆኑን ገልጸው÷ ቢያንስ ሁሉም ሰው በተመጣጣኝ ዋጋ የኪራይ ቤት እንዳያጣ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
የኮሪደር ልማት ዋና ዓላማው ያለንን ቦታ በአግባቡ እንድንጠቀም የሚያደርግ ነው፤ የኮሪደር ልማት የፈጠራ አቅም እና የኑሮ ዘዬን የቀየረ መሆኑን ጠቅሰው÷ በተሰራው ስራም አዲስ አበባ ውስጥ ከ1 ሺህ በላይ ትንንሽ ስታዲየሞች መገንባታቸውን አመላክተዋል።
የተገነቡት ትንንሽ ስታዲየሞች በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሩ ተጫዋቾችን ያበረክታሉ ሲሉም አብራርተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
 
			 
				