Fana: At a Speed of Life!

ለሦስት ሳምንት ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ተመለሰ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአቢጃታ ሐይቅ ውሃ መሙላትን ተከትሎ ለሦስት ሳምንት ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ተመለሰ።

የኃይል አቅርቦቱ የተቋረጠው በአቢጃታ ሐይቅ ውሃ መሙላትን ተከትሎ ወደ ኮስትክ ሶዳ ፋብሪካ የሚሄደው የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች በመወደቃቸው መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአዳማ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ ጣሃ አሕመድ ተናግረዋል።

የተቋረጠውን ኃይል ለመመለስ የሐይቁ ውሃ ሙሌት ፈተና እንደነበር ገልጸው÷ በአገልግሎቱ ሠራተኞችና በፋብሪካው ትብብር የኃይል መቋረጡ ትናንት ዘላቂ መፍትሔ አግኝቷል ብለዋል፡፡

መስመሩ በእንጨት ምሰሶ መውደቅ በተደጋጋሚ ኃይል መቋረጥ ይከሰት እንደነበር አስታውሰው÷ በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት የእንጨት ምሰሶዎቹን በሰባት የብረት ምሰሶ መተካቱን ተናግረዋል፡፡

ፋብሪካው ኃይል እንዲያገኝ 600 ሜትር ርዝመት ያለው የመስመር ዝርጋታ እንደ አዲስ በመስራት ስምንት ተጨማሪ የእንጨት ምሰሶ በድምሩ 15 ምሰሶዎች መተከላቸውን ነው የገለጹት፡፡

የጥገና ሥራውን የቡልቡላ አገልግሎት መስጫ ሠራተኞች ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቃቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ አቶ አንዋር አብራር ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.