Fana: At a Speed of Life!

አስከፊው የህጻናት የዓይን ካንሰር…

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሬቲኖ ብላስቶማ የሚባለው የህጻናት የዓይን ካንሰር ገና በልጅነታቸው ከ5 ዓመት በታች በሆኑ ህጻናት ላይ የሚፈጠርና ለህይወት አስጊ የሆነ ህመም ነው፡፡

ሬቲኖ ብላስቶማ የተሰኘው የህጻናት የዓይን ካንሰር ዓይን ላይ ጉዳት ከማስከተል ባለፈ ህይወትንም ሊያሳጣ የሚችልና ህመም በርካታ ህጻናትን የሚያጠቃ እንደሆነ ይገለፃል፡፡

የሚታይ ነጭ ጥላ ወይም የዓይን መንሸዋረር ብዙ ጊዜ የተለመደ ምልክት ሲሆን÷ በሺዎች የሚቆጠሩ ልጆችንም ጎድቷል፡፡

ሰዓዳ ይመር እና ውቤ ካቢሶ የሬቲኖ ብላስቶማ ዓይን ካንሰር ተጠቂ የሆኑ ህጻናት ወላጆች ናቸው፡፡

ቀደም ብለው ህመሙን ለመለየት ተቸግረው እንደነበር በማስታወስ ከዚህ በፊት ሁለቱም እናቶች በተለያዩ የህክምና አማራጮች በራሳቸው እና በቤተሰብ ድጋፍ የልጆቻቸውን ዓይን ለመታደግ ጥረት አድርገዋል፡፡

በልጆቻቸው የህክምና ወጪ የተፈተኑት ወላጆቹ÷ በኋላ ከተለያዩ ወገኖች በተሰጣቸው ጥቆማ መሠረት ወደ ተስፋ አዲስ የህጻናት ካንሰር መርጃ ድርጅት ገብተው ድርጅቱ በህክምና ክትትሉ ሂደት የነበረባቸውን ድካም እንደቀነሰላቸው ነግረውናል፡፡

በህክምና ክትትሉ ሂደትም የአንደኛው ህጻን አንድ ዓይን እንደተጎዳ እና አንዱ ግን እንደሚተርፍ በህክምና ባለሙያዎች የተረጋገጠ ሲሆን÷ ሌላኛው ህጻን ግን ሁለቱም ዓይኑ ሬቲኖ ብላስቶማ በሚባለው የህጻናት የአይን ካንሰር የተጠቁ በመሆናቸው ህመሙ ወደ ሌሎች የአካል ክፍሉ እንዳይሰራጭ ሁለቱም የተጎዱ ዓይኖች በህክምና ተወግደውለታል፡፡

በአሁኑ ጊዜም ህመሙ ታካሚ ልጆቻቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ተስፋ አዲስ የህጻናት ካንሰር መርጃ ድርጅት ውስጥ እያስታመሙ እንደሚገኙ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል፡፡

የህጻናት የዓይን ካንሰር ህመም ቀደም ብሎ ከታወቀ የሚድን ሲሆን÷ ህከምና ካልተደረገለት ግን ከዓይን አልፎ ወደ ሌሎች የሰውነት ከፍሎች ሊዛመት ይችላል፡፡

በተስፋ አዲስ የህጻናት ካንሰር መርጃ ድርጅት የፈንድ አሰባሳቢ ባለሙያ መቅደስ ከበደ እንዳሉት÷ ተስፋ አዲስ የህፃናት ካንሰር መርጃ ድርጅት ከህክምና ተቋማት ጋር በመሆን ለዓይን ካንሰር ታማሚ ህፃናት የምገባ፣ የመኝታ፣ የትምህርት እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል፡፡

በስነ ልቦና ጠንካራ ሆነው ህክምና እንዲከታተሉ ለወላጆችና ለልጆችም የተለያየ የስነ ልቦና ድጋፍ ይደረግላቸዋል ያሉት ደግሞ በድርጅቱ የሥነ ልቦና ባለሙያ መዓዛ ተሰማ ናቸው፡፡

ድርጅቱን ማንኛውም ሰው የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ፣ ልጆችን በመጎብኘት በማጫወት እንዲሁም በተለያዩ አማራጮች ድጋፍ በማድረግ እንዲያግዝም ጥሪ ቀርቧል፡፡

በየሻምበል ምህረት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.