በሳዑዲ ለሥራ የተሰማሩ ዜጎችን ደህንነትና ጥቅም ለማስከበር እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ ለሥራ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያንን ደህንነት እና ጥቅም ለማስከበር በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) እና ሌሎች የኤምባሲው አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በውጭ የሥራ ስምሪት እና በሳዑዲ ለሥራ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን መብት እና ጥቅም ማስከበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
አምባሳደር ሙክታር (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ÷ በሳዑዲ ለዜጎች የሥራ እድል ለማመቻቸት ከተያዘው እቅድ አንጻር በተደረገው ስምምነት መሰረት ሰፊ የሥራ እድል እየተፈጠረ ነው ብለዋል፡፡
ለኢትዮጵያውያን ሙያተኞች በሳዑዲ የሥራ እድል በስፋት እንዲመቻች ከባለድርሻ አካላት ጋር የተጀመረው ውይይት ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡
እድሉን አግኝተው ወደ ሳዑዲ የሚመጡ ዜጎች ደህንነታቸው ተጠብቆ የመጡለትን ዓላማ አሳክተው እንዲመለሱ በቁርጠኝነት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል፡፡
ወ/ሮ ሙፈሪሃት በበኩላቸው ÷ ከታሪካዊና መልክዓ ምድራዊ ቅርበት እንዲሁም ካለው ሰፊ የሥራ እድል አንጻር ለሳዑዲ ዓረቢያ የሥራ ስምሪት ልዩ ትኩረት እንደተሰጠው ተናግረዋል፡፡
የተያዘውን እቅድ ለማሳካትም አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ መግለጻቸውን ኤምባሲው ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!