Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም መስሕቦችን የማሻሻልና መዳረሻዎችን የማልማት ስራ በትኩረት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ የቱሪዝም መስሕቦችን የማሻሻልና መዳረሻዎችን የማልማት ስራ በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም መስሕቦችን በመለየትና በማልማት የቱሪዝም እንቅስቃሴውን ለማሳደግ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል፡፡

ክልሉ በአዲስ መልክ ከተደራጀ በኋላ የቱሪዝም እንቅስቃሴውን ለማሳደግ የመሰረት ልማትና የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ላይ በትኩረት መሰራቱን አስረድተዋል፡፡

የክልሉ የቱሪዝም እንቀስቃሴ በየዓመቱ 14 በመቶ እያደገ መሆኑን ጠቅሰው÷ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ከ452 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡

በዚህም መጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ465 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ እና ከ7 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች በክልሉ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች መጎብኘታቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪም በሩብ ዓመቱ ከ6 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጠሩን አመላክተዋል፡፡

በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም መስሕቦችን በማሻሻል እና መዳረሻዎችን የማስፋት ስራ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው÷ ለአብነትም የሀምበሪቾ ተራራን የማልማት ስራ መከናወኑን ጠቅሰዋል፡፡

ጊቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ፣ የጢያ ትክል ድንጋይ ዓለም አቀፍ መካነ ቅርስ አካባቢ ልማት እና ሌሎች የቱሪስት መዳረሻዎችን የማሻሻያ ሥራ እየተሰራላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ ከሕዝብና ባለሃብቶች ጋር በቅንጅት እየተሰራ ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡

የኮሪደር ልማት ስራዎችም ለቱሪዝም ዘርፍ ተጨማሪ አቅም እየፈጠረ መሆኑን የገለጹት አቶ ሳሙኤል÷ ዘንድሮ በክልሉ የሚከበረውን 20ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓልን ተከትሎ የክልሉን እምቅ የቱሪዝም ሃብት ለማስተዋወቅ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በወንድማገኝ ጸጋዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.