Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተደረጉ ምርምሮች ውጤት እያመጡ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፈር መሸርሸር እና በአሲዳማነት በመጠቃት ምርት የማይሰጥ መሬት በተፈጥሯዊ መንገድ እንዲያገግምና ምርታማነትን ለማሻሻል በጅማ ዩኒቨርሲቲው የተደረጉ ምርምሮች ውጤታማ ሆነዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ግብርናና እንስሳት ሕክምና ኮሌጅ የተፈጥሮ ሀብትና የአከባቢ ጥበቃ መምህርና ተመራማሪ ባዩ ዱሜ (ዶ/ር)፤ መሬትን በተፈጥሯዊ መንገድ በመንከባከብ ውጤት ማምጣት ይቻላል ብለዋል።

አፈር እንዳይታጠብ በማድረግ የእርሻ መሬትን አርሶ አደሩ በተፈጥሮ መንገድ በመንከባከብ ስንዴ በማልማት ምርታማ መሆን እንደቻለ በምርምር መረጋገጡን ተናግረዋል።

የመሬትን ለምነት የሚጠብቁ እጽዋቶች በመትከል እና እርከን በመስራት የመሬት መሸርሸርን በመቀነስ ጥሩ ምርት ማግኘት መቻሉን የዩኒቨርሲቲው መምህርና ተመራማሪ ጌትነት ሰይድ ገልፀዋል።

አርሶ አደሩ ለዚህ ስራ ምንም ወጪ ሳያወጣ በአካባቢው ባለዉ ነገር በመጠቀም በዘላቂነት የአፈር ለምነትን በመጠበቅ ምርታማነቱን ማሳደግ እንደሚችልም አስረድተዋል፡፡

በጅማ ዞን ዴዶ ወረዳ በአፈር መሸርሸር ምርት የማይሰጥ እና ለአሲዳማነት የተጋለጠ መሬትን በተፈጥሯዊ መንገድ በመጠበቅና አፈሩን በማከም በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ መሆን መቻሉ ተገልጿል።

በወረዳው አብዛኛዉ ለእርሻ የሚውል መሬት ለመሬት መሸርሸር የተጋለጠ በመሆኑ ዝቅተኛ ምርት ይሰጥ እንደነበረ ተነግሯል።

የዩኒቨርሲቲው የምርምር ስራ ለወረዳዉ አርሶ አደሮች በሰርቶ ማሳያ የተሞከረ በመሆኑ በቀጣይ በስፋት ይሰራበታል ተብሏል።

አርሶ አደሮችም ከዚህ ቀደም ከመሬታቸዉ የሚያገኙት ምርት ዝቅተኛ መሆኑን ተናግረው ተመራማሪዎቹ ባሳዩያቸዉ ዘዴ በመጠቀም ስንዴን ማልማት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡

በወርቅአፈራው ያለው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.