በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በግብርናው ዘርፍ አዳዲስ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ዘርፍ አዳዲስ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው አለ የክልሉ ግብርና ቢሮ።
በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ኡስማን ሱሩር ÷ በክልሉ የተጀመሩ አዳዲስ ኢኒሼቲቮች አርሶ አደሩን በማነቃቃት ውጤታማነቱን እያሳደጉ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
ለአብነትም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየተጠናከረ የመጣው “የፀደይ አዝመራ” እርሻ ሥራዎችን የማስፋፋት ተግባር አንዱ መሆኑን ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።
ፀደይ አዝመራ ከዚህ ቀደም በጥቂት አካባቢዎች ውስን ሽፋንና ውጤት የነበረው መሆኑን አንስተው ÷ አሁን ላይ በክልሉ በሁሉም አካባቢ ተጨማሪ የምርት ወቅት እየሆነ መጥቷል ነው ያሉት።
በወቅቱ በቆሎ በተሰበሰበባቸው ውስን የእርጥበት ቦታዎች በአጭር ጊዜ ለምርት የሚደርሰውን የሽምብራ ሰብል በብዛት እንዲሁም የጓያ ሰብል በተወሰኑ ቦታዎች ላይ የመዝራት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
ባለፈው ዓመት በፀደይ አዝመራ ወቅት ከ37 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በማልማት 750 ሺህ ኩንታል ምርት መገኘቱን አስታውሰዋል፡፡
በተያዘው ዓመትም ከ60 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በማልማት ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
ይህም መነሳሳትና ትጋት መንግሥት ድህነትን ለመቀልበስ ቁልፉ ግብርናን ማዘመንና ውጤታማነትን ማሳደግ ብሎ ያስቀመጣቸው ትልሞች ትክክለኛነት ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የአዲስ እሳቤ ውጤት የሆነው የፀደይ አዝመራ የሥራ ባህል ለውጥ፣ የመሬት ምርታማነት መጨመር፣ የጊዜ ምርታማነትና ባልተለመደ ወቅትና በትንሽ እርጥበት አምርቶ ሃብት መፍጠር መቻልን ያሳየ መሆኑንም አስረድተዋል።
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!