የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን መርሐ ግብር ለአየር ንብረት ተፅዕኖ የማይበገር ግብርናን ዕውን ለማድረግ ይሰራል
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ግብርና ትራፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን መርሐ ግብር ለአየር ንብረት ተፅዕኖ የማይበገር ግብርናን ዕውን ለማድረግ ይሰራል አሉ።
የ2ኛው ምዕራፍ የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን መርሐ ግብር ማስጀመሪያ መድረክ ላይ ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ መርሐ ግብሩ የግብርና ዘርፍን ዓቅም ተጠቅሞ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ሂደትን ያፋጥናል።
ኢትዮጵያ ስማርት የአየር ንብረትን መሰረት ያደረገ የግብርና እድገትን በማሳካት አርሶ አደሮችን፣ ወጣቶችንና ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ መርሐ ግብሩ ጥረት ያደርጋል ብለዋል።
መርሐ ግብሩ የመጀመሪያው ምዕራፍ የነበሩ የምርት ዓይነቶችን እና ተደራሽነትን ወደ ዘጠኝ ክልሎች በማሳደግ እንደሚተገበር ጠቁመዋል።
የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደግ እና ለአየር ንብረት ተፅዕኖ የማይበገር የግብርና ዘርፍን ዕውን ማድረግ የመርሐ ግብሩ ትኩረት መሆኑን አንስተው፤ የፋይናንስ አማራጮችን ለማሳደግ እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።
በገጠር ትራንስፎርሜሽን ላይ የተመሰረተውን የግብርና ዘርፍ ትራንስፎርሜሽንን ከግብ ለማድረስ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ሱነ ግሮግስትሩፕ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ግብርናውን ለማዘመን የምትሰራውን ስራ ሀገራቸው ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸዋል።
በግብርና ኮሜርሻላይዜሽን መርሐ ግብር የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ የመጣውን ለውጥ አድንቀዋል።
የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ለኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የሰጠው ሽልማት የተመዘገበው ውጤት ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።
ለሁለተኛው ምዕራፍ ትግበራ ዴንማርክ ከ79 ሚሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ እንደምታደርግም ይፋ አድርገዋል።
በመሳፍንት ብርሌ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!