Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ሁለተኛ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ19ኛው የአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለተኛ የወርቅ ሜዳሊያ አስመዝግባለች።

64 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር በሸፈነው የአዳጊ ወጣቶች የጎዳና ላይ ውድድር፣  በሴቶች ብስክሌተኛ ፅጌ ካህሳይ ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቅቃለች።

ፅጌ ካህሳይ ትላንት በተደረገው የግል ሰዓት ሙከራ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ማሸነፏ ይታወቃል።

ቅሳነት ግርማይ ሦስተኛ እንዲሁም ራሄል ታመነ አራተኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን አጠናቅቀዋል፡፡

በ2025 የአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮና ከ30 ሀገራት የተወጣጡ ብስክሌተኞች እየተካፈሉ ሲሆን ኢትዮጵያ ሁለት የወርቅ እና አንድ የነሃስ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

በወርቅነህ ጋሻሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.