የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በተለያዩ አከባቢዎች ያካሄዱት የልማት ሥራ ጉብኝት…
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በተለያዩ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
አመራሮቹ ባለፉት ቀናት በ2ኛ ዙር “የመደመር መንግሥት ዕይታ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሃሳብ የተሰጠውን ሥልጠና ሲወስዱ ቆይተዋል፡፡
በዛሬው ዕለትም በሰለጠኑባቸው አካባቢዎች በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎችን፣ በክላስተር የለማ ስንዴ ማሳን እና ሌሎች የደረሱ የመኸር ሰብሎችን ተመልክተዋል፡፡
እንዲሁም የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታን እና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡