ኮፕ32 ኢትዮጵያን ለዓለም ለማሳየት ትልቁ መድረክ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባኤ (ኮፕ32) የቱሪዝም ሀብታችንን ለዓለም ለማሳየት ትልቁ መድረክ ነው አሉ፡፡
ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ኮንቬንሽን መሠረት የኮፕ32 አስተናጋጅ ሀገር ሆና መመረጧ ይታወሳል፡፡
የኮፕ32 የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በዛሬው ዕለት ቁልፍ የዝግጅት ተግባራትን ለማቀናጀት የሚያስችል ስብሰባ አድርጓል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ኮፕ32 ኢትዮጵያን ለዓለም ለማሳየት የሚያስችል ትልቅ መድረክ ነው፡፡
በሦስት ዓመት ከግማሽ ጉዟችን የመጀመሪያ ዓላማ የሀገር ግንባታ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በዚህ ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ መሰረታዊ ለሆኑ ጉዳዮች ብቁ መሆኗን አስተማማኝ በሆነ መንገድ ማስጨበጥ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በሀገር ግንባታ ሂደቱ ውስጥ የተቋቋመው የመሰረተ ልማት በርካታ ስራዎች እንደሚጠበቅበት ጠቅሰው፥ ይህ ስራ ስኬታማ እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
የሀገር ገጽታ ግንባታ ሁለተኛው ዋና ዓላማ መሆኑን ገልጸው፥ ኢትዮጵያ ጥሩ ሀገር ናት ከማለት ባለፈ ጥንታዊና በርካታ የሚታይ ባህልና ታሪክ ያላት ሀገር እንደመሆኗ ከቱሪዝም አንጻር ያላትን ሀብት ለዓለም ለማሳየት ትልቁ መድረክ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በዚህም የኢትዮጵያን ገጽታ ለዓለም ለማሳወቅ የሚያስችል ስራ የምንሰራበት ጊዜ ነው ብለዋል፡፡
ሀገር በመገንባት የኢትዮጵያን ገጽታ ለዓለም ከማሳወቅ ባሻገር የሚያሰባስቡን ጉባኤዎች ስኬታማ ሊሆኑ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡
በኃይለማርያም ተገኝ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!