ብሔራዊ ባንክ በአዲሱ የባንክ አዋጅ መሰረት ለስታንዳርድ ባንክ አዲስ ፈቃድ ሰጠ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ብሔራዊ ባንክ በተሻሻለው የባንክ ንግድ አዋጅ መሠረት ለስታንዳርድ ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ቢሮ አዲስ ፈቃድ ሰጥቷል።
ፈቃዱ የተሰጠው የውጭ ባንክ ተወካይ ቢሮዎች ፈቃድና ቁጥጥር በቀጥታ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ስር እንዲሆኑ በተደነገገው የተሻሻለው ሕግ መሰረት ነው።
በዚህም ባንኩ የተወካይ ቢሮዎች በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተሰጣቸውን ፈቃድ በማደስ አዲስ ፍቃድ የመስጠት ስራ ጀምሯል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ በውክልና ቢሮው በኩል የሚንቀሳቀሰው ስታንዳርድ ባንክ በአዲሱ የቁጥጥር ማዕቀፍ መሰረት ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ያገኘ የመጀመሪያው የውጭ ተቋም መሆን ችሏል።
ፈቃድ የሚሰጣቸው የውክልና ቢሮዎቹ ለውጭ ባንኮች የግንኙነትና የንግድ መረጃ ማዕከላት በመሆን የገበያ ጥናቶችን በማካሄድ፣ የንግድ ግንኙነቶችን በመገንባትና በማስተዋወቅ ያገለግላሉ።
እነዚህ የውክልና ቢሮዎች በባንክ አገልግሎቶችም ሆነ በገንዘብ ዝውውር አገልግሎት ውስጥ የሚሳተፉ አለመሆናቸውን ባንኩ ለፋና ዲጅታል በላከው መረጃ አመላክቷል።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!