ማዕድንና ኢንዱስትሪ መስፈንጠሪያ፤ ዲጂታል ኢኮኖሚ ደግሞ ማስተሳሰሪያ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ማዕድን እና ኢንዱስትሪ ዘርፎች መስፈንጠሪያ፤ ዲጂታል ኢኮኖሚ ደግሞ ማስተሳሰሪያ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‘በመደመር መንግሥት ዕይታ የዘርፎች እመርታ’ በሚል ርዕስ ለብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በሰጡት ስልጠና ላይ እንዳሉት፤ የማዕድን ዘርፍ ፈጣን እና ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማምጣት ለመስፈንጠር ያግዛል።
ዘርፉ አጠቃቀምን በዕውቀት እና በታቀደ መንገድ ጥንቅቅ ያለ ስራ መስራት እንደሚጠይቅ ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ የጋዝ፣ የማዳበሪያ፣ የመስታወት እና የኢነርጂ ሀብቷ የተከበረች ሀገር እንደሚያደርጋት ገልጸው፤ የውጭ ምንዛሪ ፍላጎትን ለማሟላት ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል።
በፈቃድ አሰጣጥ ረገድ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።
የኢንዱስትሪ ዘርፍ ገቢ ምርቶችን መተካት፣ ወጪ ንግድ እና ሌሎች ዘርፎችን የሚያግዝ ግብዓት ማምረት የሚሉ ሦስት ዓላማዎች እንዳሉት ጠቁመዋል።
ዘርፉ ከመዛባት ወደ ማንሰራራት እንዲያድግ በቅርበት በመምራት የግሉ ዘርፍ የሚሰራበትን አስቻይ ሁኔታ እና ሚዛናዊ ትብብር በመፍጠር እድገትን ማምጣት እንደሚገባ ገልጸዋል።
ዲጂታል ኢኮኖሚ አስተሳሳሪ በመሆኑ ቴክኖሎጂን በከፍተኛ ደረጃ ማስፋፋት እንደሚያስፈልግ አንስተው፤ ዘመኑን በዋጀ መልኩ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል።
በመሆኑም ዲጂታል መታወቂያ፣ ሞባይል ተጠቃሚነት እና ዘመናዊ የክፍያ ዘዴን ማሳደግ ወሳኝ እንደሆነ አስገንዝበው፤ ማዕድን እና ኢንዱስትሪ ዘርፎች መስፈንጠሪያ፤ ዲጂታል ኢኮኖሚ ደግሞ ማስተሳሰሪያ መሆናቸውን አብራርተዋል።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!