ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 14 ፣ 2012 (ኤፍ. ቢ.ሲ)ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል።
ለፕሬዝደንቷ የሹመት ደብዳቤ ያቀረቡት የግሪክ፣ የጀርመን፣ የሱዳን እና የሞሪታኒያ አምባሳደሮች ናቸው።
አምባሳደሮቹ የሹመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅት÷በየሀገሮቻቸውና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ መናገራቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።