Fana: At a Speed of Life!

ሕብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ማጠናከር ዘመኑ የሚፈልገው አርበኝነት ነው – አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሕብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ማጠናከር ዘመኑ የሚፈልገው አርበኝነት ነው አሉ በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር)፡፡

የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አቡዳቢ በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት ተከብሯል፡፡

አምባሳደር ጀማል (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ÷ ኢትዮጵያን በየዘመኑ ዋጋ ካስከፈሏት ተግዳሮቶች ውስጥ አክራሪ ብሔርተኝነትና ከፋፋይ አጀንዳ ተጠቃሾች ናቸው ብለዋል፡፡

ለሁላችንም የምትመች እና የበለጸገች ሀገር እንድትኖረን በመግባባት ላይ የተመሰረተ የጋራ ትርክት መገንባት ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

ከአንድነት ይልቅ ልዩነታችን ላይ ትኩረት ያደረገውን የፖለቲካ ባሕል እንዲሁም አሁን ላይ በተለያዩ ሚዲያዎች የሚቀነቀነውን የተሳሳተ ትርክት መጋፈጥ ዘመኑ የሚፈልገው አርበኝነት ነው ብለዋል፡፡

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ለሀገራቸው የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘንድሮ ለ7ኛ ጊዜ የሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ የኢትዮጰያን ቁመና በሚመጥን መልኩ በስኬት እንዲጠናቀቅ መንግስት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡

መርሐ ግብሩ የኢትዮጵያን ብዝሃነት በሚያንጸባርቅ መልኩ በብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህላዊ ምግቦች፣ ባህላዊ አልባሳትና በሕጻናት ትርዒት በድምቀት መከናወኑን ኤምባሲው ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡

በአከባበር ሥነ ሥርዓቱ ከልዩ ልዩ የአቡዳቢ ግዛቶች የተሳበሳቡ የኢትዮጵያውያን ማሕበረሰብ አባላት፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ሕጻናት ታድመዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.