በአዲስ አበባ የተከናወነው የልማት ሥራ ከተማዋን ውብና ምቹ አድርጓታል – አርቲስት ኦሞ ሳንጋሬ
አዲስ አበባ፣ ታሕሳስ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም አቀፍ ዝናን ያተረፈችው ማላዊቷ አርቲስት ኦሞ ሳንጋሬ በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውራ ተመልክታለች፡፡
አርቲስት ኦሞ ሳንጋሬ የግራሚ አዋርድ ሽልማት አሸናፊ፣ የአፍሪካ ሴቶች መብት ተከራካሪ እና ዓለም አቀፍ ዝናን የተጎናጸፈች ድምጻዊት ናት።
በእናቷ በኩል የኢትዮጵያ የዘር ሐረግ እንዳላት የምትናገረው ኦሞ ሳንጋሬ ፥ የእንጦጦ ፓርክን፣ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝዬምን፣ የመንገድ መሰረተ ልማት እና ፓርኮችን ጨምሮ ሌሎች የልማት ሥራዎችን ተመልክታለች።
አርቲስቷ በጉብኝቷ ወቅት በሰጠችው አስተያየት÷ ከአምስት ዓመታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ መጥታ እንደነበር አስታውሳለች፡፡
አሁን ላይ የከተማዋ በፍጥነት መለወጥ እና በራስ አቅም ይህን የመሰለ ከተማ እንዲሁም ጥራት ያለው ሕንጻ መገንባት አስደናቂ ነው ብላለች።
በከተማዋ ከተመለከተችው ዕድገት ጋር የተሰሩ የተለያዩ ፓርኮች እና የመዝናኛ ቦታዎች የሚደነቁ መሆናቸውን አስረድታለች።
በጉብኝቱ ከበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ አርቲስቶች፣ ቲክቶኮሮች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችም ተሳትፈዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!