Fana: At a Speed of Life!

የፋይዳ መታወቂያ መተማመንን መፍጠሪያ ነው – አቶ ዮዳሄ አርዓያሥላሴ

አዲስ አበባ፣ታሕሳስ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በመላ ሀገሪቱ ከ29 ሚሊየን በላይ ዜጎች የፋይዳ መታወቂያ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል አሉ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ አርዓያሥላሴ።

ዋና ዳይሬክተሩ ከፋና ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት፥ አንድ ሰው አንድ ማንነት ብቻ እንዲኖረው ለማስቻል እየተሰራ ነው፡፡

የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም እስከ ሰኔ 30 ድረስ የፋይዳ መታወቂያ ተገልጋዮችን ቁጥር ወደ 90 ሚሊየን ለማድረስ አቅዶ እየሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የፋይዳ መታወቂያ በማንኛውንም አይነት የውል፣ የብድርና ሌሎች አገልግሎቶች በአገልግሎት ሰጭና ተቀባይ መካከል መተማመንን ለመፍጠር ያለመ ነው ብለዋል።

ከአንድ በላይ የተንቀሳቃሽ ስልክ መስመር ያላቸው ግለሰቦች ሲም ካርዳቸውን በመጠቀም የሚፈጽሙትን የማጭበርበር ወንጀል ለመከላከል የፋይዳ አገልግሎት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን መረጃን የማጥራት ሥራ በሰፊው መሥራት መጀመሩንም አንስተዋል።

በቀጣይም የፋይዳ መታወቂያን ከሌሎች አገልግሎቶች ጋር በማስተሳሰር በሕዝብ መካከል መተማመንና የአገልግሎት ቅልጥፍናን ለማምጣት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.