የዓለም ንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል በሰባት ወራት የተከናወኑ ድርድሮች ታሪክ የቀየሩ ናቸው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም ንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል በሰባት ወራት የተከናወኑ ድርድሮች ታሪክ የቀየሩ ናቸው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።
“ኢትዮጵያን በንግድ በማስተሳሰር ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር” በሚል መሪ ሐሳብ የዓለም የንግድ ድርጅት አባልነትን ሂደትን የተመለከተ መድረክ ተካሂዷል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ ወደ ዓለም ንግድ ድርጅት ለመቀላቀል ባለፉት ሰባት ወራት ያከናወነችው ተግባር በ22 ዓመታት የተደረገውን ጥረት ወደ ልዩ ምዕራፍ ያሸጋገረ ነው፡፡
በ5ኛው እና 6ኛው የሥራ ቡድን ስብሰባዎች የተመዘገቡ ውጤቶች የመፈጸም ውስጣዊ አቅማችንን በጉልህ ያሳዩ ናቸው ብለዋል፡፡
በተለይም በ6ኛው የሥራ ቡድን ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ የእስካሁኑ የሥራ ቡድን ስብሰባ ሪፖርት ሒደቱን አንድ ርምጃ ከፍ ማድረጉን ገልጸው÷ በዚህም የባለብዙ ወገን የድርድር ምዕራፍ መቋጫ ላይ ደርሰናል ሲሉ ተናግረዋል።
በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም የሀገሪቱን ውስጣዊ የኢኮኖሚ ማነቆዎች ለመፍታት በተወሰዱ ማሻሻያዎች ለውጥ ማምጣት መቻሉን አንስተው÷ በዚህም ኢትዮጵያ ዳግም ወደ ጄኔቫ የድርድር መድረክ መመለሷን ነው የገለጹት፡፡
ሀገራችንን የዓለም አቀፉ የንግድ ሥርዓት አካል ለማድረግ እስካሁን የነበረው ሂደት ያዝ ለቀቅ ተደርጎ ሲመራ ነበር ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ በለውጡ ማግስት ይህ አካሄድ መቀየሩን አስረድተዋል፡፡
ድርድሩ ባጠረ ጊዜ እንዲጠናቀቅ መንግሥት አቅጣጫ ማስቀመጡን ጠቅሰው÷ ለድርድሩ የሚያስፈልጉ ሂደቶች እና ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።
ለአብነትም ብሔራዊ የድርድር እና ቴክኒክ ኮሚቴ በአዲስ መልክ መደራጀቱን ጠቁመው÷ በተለያየ ማዕቀፍ ሥልጠና የመስጠትና የአቅም ግንባታ ሥራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል፡፡
ከአባል ሀገራት ለቀረቡ ጥያቄዎች የሀገሪቱን ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ ምላሽ መሰጠቱን አመልክተዋል፡፡
የመንግሥት አስፈጻሚ ተቋማት ከሕግ ማዕቀፍ እስከ አተገባበር ከዓለም ንግድ ድርጅት የሕግ ማዕቀፍ ጋር የተጣጣመ ስለመሆኑ በፍጥነት በማረጋገጥ ምቹ የአሰራር ሁኔታዎችን ተግባራዊ በማድረግ መንግሥታዊ ሥራና ኃላፊነትን ለመወጣት ዝግጅታቸውን እንዲያጠናቅቁም አሳስበዋል፡፡
በለይኩን ዓለም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!