በኢትዮጵያ የዳበረ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ እንዲጎለብት እየተሠራ ነው
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የዳበረ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት የፖለቲካ ፓርቲዎች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ናቸው አለ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርትዎች የጋራ ምክር ቤት።
ምክር ቤቱ ያዘጋጀው ”የፖለቲካ ተሳትፎ መመሪያ መጽሐፍ” ተመርቋል።
የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ምክር ቤቱ በሀገሪቱ ጠንካራ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የበኩሉን አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው።
የፖለቲካ ፓርቲዎች ብቁና ዝግጁ ሆነው በሀገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ጠንካራ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚያስችል የፖለቲካ ተሳትፎ መመሪያ መጽሐፉ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
ጠንካራ እና አማራጭ እሳቤን ማቅረብ፣ የተሳካ የሕዝብ ግንኙነትን በሚገባ መተግበር፣ የአካታችነትና አሳታፊነትን ባህል መገንባትን ጨምሮ ለስኬታማ የፖለቲካ ምህዳር ወሳኝ የሆኑ ሰፋፊ ተግባራትን እንደሚያጠቃልልም አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋዬ ንዋይ በበኩላቸው፤ የመመሪያ መጽሐፉ ፓርቲዎች በምርጫ ሂደት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲሁም የውስጠ ፓርቲ አስተዳደር መያዙን ጠቅሰዋል።
በመሆኑም የፖለቲካ ፓርቲዎች በመደበኛ ጊዜያቸው ከሚያከናውኗቸው ተግባራት በተጨማሪ ለሀገራዊ ምርጫ ተሳትፏቸው አጋዥ መሆኑን ጠቁመዋል።
መጽሐፉ በፖለቲካ ፖርቲዎች መካከል የሚፈጠሩ ችግሮች ቶሎ እንዲፈቱ የምርጫ ቅስቀሳ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ቀድሞ በመለየት መፍትሔ ለማስቀመጥና የፖለቲካ አለመግባባቶች ወደ ግጭት እንዳያመሩ ለማድረግ እንደሚያግዝ ጠቅሰዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች መመሪያ መጸሐፉን በመጠቀም እና በማዳበር ለሀገሪቱ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ መጠየቃቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
በተጨማሪም የፖለቲካ ፓርቲዎች ከጋራ ምክር ቤቱና እርስ በእርስ ስለሚኖራቸው ግንኙነት በተመለከተ የፖለቲካ ተሳትፎ መመሪያ መጽሐፉ ሐሳቦች መያዙን ተናግረዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!