Fana: At a Speed of Life!

የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች…

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፖሊዮ መከላከያ ክትባት በተለያዩ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በዛሬው ዕለት መሰጠት ጀምሯል፡፡

ክትባቱ በማዕከላዊ ኢትዮጵያና አፋር ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነው በዘመቻ መልክ እየተሰጠ የሚገኘው፡፡

የአፋር ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ ያሲን ሓቢብ እንዳሉት ÷ ከፖሊዮ መከላከያ ክትባት ዘመቻው ጎን ለጎን ሌሎች ክትባቶች ይሰጣሉ፡፡

ክትባቱ በሁሉም ጤና ተቋማት ጊዜያዊ የክትባት ማዕከላት እንደሚሰጥ ጠቁመው ÷ የቤት ለቤት ዘመቻ እንደሚካሄድም ተናግረዋል፡፡

በተለይ በአርብቶ አደር አካባቢዎች የሚገኙ ሕጻናትን ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ነው የገለጹት፡፡

በተመሳሳይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሕጻናት የፖሊዮ ክትባት መስጠት መጀምሩን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) ክትባት ዘመቻ በዛሬው ዕለት መሰጠት መጀመሩ ተመላክቷል፡፡

ስለሆነም ከዛሬ ጀምሮ እስከ ታሕሣሥ 6 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደው የፖሊዮ ክትባት በስኬት እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ተጠይቋል፡፡

በካሊፋ ካድሪ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.